የአርባምንች መካነ ኢየሱስ ቴክኒክ ኮሌጅ በሶላር ኢነርጂ ያሠለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ

የአርባምንች መካነ ኢየሱስ ቴክኒክ ኮሌጅ በሶላር ኢነርጂ ያሠለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ

የአርባምንች መካነ ኢየሱስ ቴክኒክ ኮሌጅ በሶላር ኢነርጂ ያሠለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ

የአርባምንጭ መካነ ኢየሱስ ቴክኒክ ኮሌጅ ከኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ደቡብ ምዕራብ ሲኖዶስ ልማትና ማኅበራዊ አገልግሎት ኮሚሽን (DASSC) እና የአድቨንቲስት ልማትና ተራድዖ ድርጅት (ADRA) ከተሰኙ መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ባለፉት ሦስት ወራት በአጫጭር ሥልጠና ያሠለጠናቸውን 38 ተማሪዎች አስመረቀ። ፕሮጀክቱ በሦስት ዙሮች ለ120 ተማሪዎች የሥልጠና ዕድል የፈጠረ ሲሆን የአሁኑ ተመራቂዎች የጀመጀመሪያ ዙር ሠልጣኞች መሆናቸው ተገልጿል። ሠልጣኞቹ በቆይታቸው የጸሐይ (ሶላር) ቴክኖሎጂ ዲዛይን, ተከላ, አሠራር እና ጥገና፥ እንዲሁም በተጨማሪ፣የሥራ ፈጠራና የሥራ ፍለጋ ክህሎቶች ሠልጥነው በአግባቡ ከጨረሱ በኋላ የተለያዩ ባለ ድርሻ አካላት በተገኙበት ተመረቀዋል። ሥልጠናው በአርባምንጭ መካነ ኢየሱስ ቴክኒክ ኮሌጅና በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሶላር ኢነርጂ ዲፓርትመንት ጋር በመተባበረ የተሰጠ መሆኑ ተገልጿል። ከተመረቊት 38 ተማሪዎች መካከል 13ቱ የሥራ ላይ ልምምድ (Internship) ለማድረግ Solar Village ከተሰኘ ተቋም ጋር ተቀላቅለው ሥራ መጀመራቸው ተገልጿል። ከ13 ተመራቂዎች 3ቱ ወላይታ ዞን፣ 3ቱ ጋሞ ዞን ዳራማሎ ወረዳ፣ 3ቱ ደቡቦ ኦሞ የሄዱ ሲሆን 4ቱ ወደ ቡርጂ ዞን መሄዳቸው ታውቋል።

Comments

No comments yet. Why don’t you start the discussion?

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *